አካዳሚው በተለያዩ ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች ላይ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሠራሮችን ለማጎልበት የወርሐዊ ገለፃ፣ የፓናል ውይይትና ምሁራዊ የክርክር መድረኮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
በዚሁ መሠረት ”በዘረመል ምህንድስና ዘዴ የሚመረቱ የግብርና ምርቶች ጥቅሞችና ስጋቶች”፣ (The Benefits and Risks of Genetically Modified Organisms) በተሰኘ የመወያያ ርእስ ዙሪያ በዘርፉ በርካታ ጥናቶችና ምርምሮችን ያደረጉ ምሁራን አወያይ በሚያነሷቸው ጥያቄዎች መሰረት በዘረመል ምህንድስና ዘዴ ተመርተው ጥቅም ላይ የሚውሉ የግብርና ምርቶች ያስከትላሉ ተብሎ ስለሚታሰቡ ጉዳቶችና በሚያስገኟቸው ጥቅሞች ዙርያ ተመራማሪዎች አተያያቸውን በሳይንሳዊ መረጃ አስደግፈው በሁለት ጎራ ተከፍለው ሙያዊ ማብራሪያ ይሰጣሉ።
መርሐግብሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ እሸቱ ጮሌ መታሰቢያ አዳራሽ ሐሙስ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ይካሄዳል።
Megenagna, Ethiopian Institute of Agricultural Research
+ 251 91 174 4540